በቤተ መቅደሱ እድሳት የበኩላችንን አስተዋጽኦ እያደረግን ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቃል ኪዳን እንሳተፍ
በየዘመናቱ የማያምኑ ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ የሚሆን ጽሑፍ
በሰንበት ትምህርት ቤቱ የበጎ አድራጎት አገልግሎት በ1983 ዓ.ም እንደተጀመረና ከ1980 ዓ.ም በፊት ከደብሩ ምግባረ ሠናይ ጋር በመጣመር በአንድነት የተቸገሩትን የመርዳት ሥራዎችን ይሠራ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ አባላት ይናገራሉ፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ሆነው መማር እየፈለጉ በዐቅም ማነስ ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ፤ ሥራ ለመጀመር መነሻ ገንዘብ ለተቸገሩ፤በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እገዛ የሚፈልጉ አባላትን ለመርዳት በተደረገ መነሻነት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ከሃምሳ ሳንቲም ጀምሮ በሚደረግ መዋጮና ከተከታታይ ትምህርት ተማሪዎች በሚደረግ ድጋፍ እንዲሁም ከቤተ ክህነት መጽሐፍ ቅዱስ በማምጣት እየተሸጠ ክፍሉን እንደተቋቋመና አገልግሎቱ እንደተጀመረ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በመዝሙርና ኪነ ጥበብ ዋና ክፍል ውስጥ ካሉት አገልግሎቶች አንዱ የሥዕል ትምህርት ነው፡፡ ትምህርቱ መሠጠት የተጀመረው በ 2000 ዓ.ም 10 በማይሞሉ ልጆች ነበር ፡፡ ዋናው ዓላማ አድርጎ የተነሳው ልጆች ሥዕል መሳል ስለሚወዱ በሥዕል ትምህርት ምክንያት የሚመጡ ልጆቹን የቤተክርስቲያንን ትምህርት እንዲማሩና በቃለ እግዚአብሔር ተኮትኩተው እንዲያድጉ የቤቱ አገልጋይ እንዲሆኑ ማስቻል ነበር፡፡
የመዝሙርና ኪነጥበብ አገልግሎት
በሰንበት ትምህርት ቤቱ ምሥረታ ታሪክ ውስጥ ከ 1954 ዓ.ም ጀምሮ የነበረ እንደሆነ የጽሑፍና የምስልማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በጊዜው መሠረታዊ ዓላማ አድርጎ
የተነሳው በመዝሙርና ኪነ ጥበባዊ ሥራዎች በዘመኑ ከነበሩት የተለያዩ ቤተ እምነቶችና እንግዳ ትምህርት ምዕመናንን በተለይም ወጣቶችን
ለመጠበቅና በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነታቸው ለማጽናት እንደነበረ ከታሪክ ለመረዳት ተችሏል።
‹‹ስለመናፍቃን መነሳት እግዚአብሔርን እናመሰግናለን›› እንዲሉ አበው በትምህርት
ቤቱ ውስጥ ከነበረው የፕሮቴስታንቶች እንቅስቃሴ የተነሳ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ ባደረው መንፈሳዊ ቅናት የዕቅበተ እምነት
አገልግሎት ለመስጠት፤ ወደ ሰ/ት/ቤት መሄድ የማይፈቀድላቸው ተማሪዎች በሳምንት አንድ ቀን ከትምህርት በኃላ ጉባኤ መካፈል እንዲችሉ
ዕድሉን ለማመቻቸት እንዲሁም ክርስቲያን ተማሪዎች በትምህርታቸው እርስ በእርስ የሚረዳዱበትን መንገድ ለመፍጠር በዚህም የሰ/ት/ቤቱ
የቀለም ትምህርት ላይብረሪ ቀን ቀን እየተከፈተ የማትሪክ ዝግጅት በሕብረት ይደረግ ነበር በጥቂት ወንድሞች አነሣሽነት ጉባኤው በ12
አባላት በ2001 ዓ.ም. አንደገና ተመሠረተ።
ቀደም ሲል በደብሩ አመሠራረት
ታሪክ ውስጥ የተገለጸው የአብነት ትምህርት እየተዳከመ የመጣ ቢሆንም አሁንም በግል ጥረታቸው በደብሩ ግቢ የተጠናከረ ባይሆንም ትምህርቱ
እየተሠጠ ይገኛል፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤቱም ትምህርቱን ለመስጠት ቢጀመርም በተማሪዎች መዳከምና የሚያስፈልገውን
ትኩረት ባለማግኘቱ በተለያዩ ጊዜያት ተጀምሮ ተቋርጧል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ የልዳው ፀሐይ፣ የፋርስ ንጉሥ፣ የቤሩት ኮከብ፣ የኢትዮጵያ ገበዝ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀገረ ኢትዮጵያ እጅግ ተወዳጅ ጻድቅ ነው፤ ለምን ብለን ስንጠይቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክርስቲያናዊ ተጋድሎ ራሱን ችሎ የሚጠቀስ ምክንያት ሲሆን በተለይም ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያውያን እምነትና ተጋድሎ ጋር የተያያዙ መነሻዎች እንዳሉት እንገነዘባለን። የክርስትና ዕምነትን በሚከተሉ ህዝቦች በተለይም የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ባሉበት ሀገር ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ደራጎንን በጦር ወግቶ በመግደል ቤሩታዊትን ከሞት ማዳኑን የሚያሳይ ስዕል በየቤተክርስቲያኑ በየምዕመናኑ ቤት ይገኛል፤ ከዚህ ባለፈ በሰማዕቱ ስም እጅግ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ታንጸዋል ”በሀገራችን እስከ 2005ዓ.ም ድረስ ከ2123በላይ የሆኑ በስሙ የታነፁ ቤተ ክርስቲያኖች አሉት፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ተወዳጅ እንደሆነ የሚያመለክት ሌላው ምስክርም፦ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ዝክር የሚዘክሩ፣ ጽዋና ማኅበር የሚጠጡ አሉ፤ ዕድርና እቁብም ይጠቀሳሉ (ቅዱስ ጊዮርጊስ መረዳጃ ዕድር)፤ በስሙ የተሰየሙ ድርጅቶችና ማኅበራት በርካቶች ናቸው፡ ከብዙ በጥቂቱ፦ መዝሙር ቤቶች፣ ሜዲካል ኮሌጅ፣ ዱቄት ፋብሪካ፣ ስፖርት ክለብ፣ ሕንፃ መሳሪያ፣ማተሚያ ቤት፣ ክሊኒክ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። በተጨማሪም የልጆቻቸዉን ስም፡- ገብረ ጊዮርጊስ፣ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ሀብተ ጊዮርጊስ፣ ተክለ ጊዮርጊስ፣ ወለተ ጊዮርጊስ….በማለት ይሰይማሉ (ይጠራሉ)፡፡ (ጊዮርጊስ ተብሎ የሚጠራም አለ)፡፡ ከዚህ ሌላም ለሹመትና ማዕረግ ዐምደ ጊዮርጊስ፣ ሰምረ ጊዮርጊስ፣ ገባባ ጊዮርጊስ፣ አጽመ ጊዮርጊስና የመሳሰሉ ይጠቀሳሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቀጥሎ ለቅዱ ጊዮርጊስ አስራት ተሰጥታለች፤ ከዚህ በተገናኘም በዐድዋ ጦርነት ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ይዘዉ በመዋጋት የሀገርን ጠላት ድል አድርገዋል፡፡ ይህም በየዓመቱ የካቲት 23 ቀን(የዐድዋ በዓል)ይከበራል፡፡
ከኢትዮጵያ ዉጭ በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም በሌሎች ሀገሮች” በሶርያና በእስክንድርያ ታላላቅ ገዳማት ሲኖሩት በምዕራብ ሩሲያ/ አሮጌ የሩሲያ ከተማ/፣ በእንግሊዝ (ለንደን በምስራቁ በኩልበ1714እና1729 /እ.ኤ.አ/ መካከልየተገነባ፣ በቤሩት (ጁኒደራጎንን የያዘበት ቦታ)፣ ፍልስጥኤም (ልዳ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ኬፕታውን)፣ በሶርያ (ይድራስ)፣ አርመን እና በመሳሰሉት ሀገራት የሚገኝና “የመንግሥታችን ጠባቂ”በሚል ቅፅል ስም ሁሉ እንደሚጠሩት የተለያዩ መዛግብቶች ያሳያሉ። የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣን ተራዳኢነት ለሀገራችን ኢትዮጵያ ይሁን፡፡